በዳያስፖራ ፖሊሲ፣ አዋጅና ደንብ ዙሪያ ለባለድርሻ አካላት ስልጠና ተሠጠ

E-mail Print PDF

በዳያስፖራ ፖሊሲ፣ አዋጅና ደንብ ዙሪያ ለባለድርሻ አካላት ስልጠና ተሠጠ

የአብክመ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት በዳያስፖራ ፖሊሲ፣ አዋጅና ደንብ ዙሪያ ለባለድርሻ አካላት የካቲት 10/2010 ዓ.ም በደብረ ታቦር ከተማ ስልጠና መስጠቱን አስታወቀ፡፡

ስብሰባውን በንግግር የከፈቱት የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ም/ኃላፊ አቶ ተሠማ ደምሴ እንደገለጹት የክልሉ መንግስት በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን በክልላቸው በተለያዩ የልማት መስኮች የሚያደርጉትን ተሳትፎ ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፤ በመሆኑም ጥሪ የተደረገላችሁ ባለድርሻ አካላት በዳያስፖራ ፖሊሲ፣ አዋጅና ደንብ ዙሪያ በሚገባ በመገንዘብ የነቃ ተሳትፎ እንድታደርጉ በማለት አሳስበዋል፡፡

የስልጠናውን ጹሑፉ ያቀረቡት የዳያስፖራ፣ ህዝብ ግንኙነትና ፕሮቶኮል ጉዳዮች ኃላፊ አቶ አውላቸው ማስሬ እንደገለጹት የዳያስፖራ ፖሊሲው የተዘጋጀው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የውጭ ጉዳይና አገራዊ ደህንነት ፖሊሲና ስትራቴጂን መነሻ በማድረግና በዳያስፖራው ጉዳዮች ዙሪያ የቆዩ መመሪያዎችንና አፈፃፀሞችን በዝርዝር በማጥናት፣ የተለያዩ ጽሁፎችንና የተሞክሮ ልውውጥ መድረኮችን እንዲሁም የሌሎች አገሮች ጠቃሚ ልምዶችን በግብአትነት በመጠቀምና ከዳያስፖራው የተሰጡ አስተያየቶችን በማካተት ነው ብለዋል ፡፡

ይህ ፖሊሲ የአገሪቱን ልማትና የዴሞክራሲ ስርዓት ለማስቀጠል ጠንካራ የዳያስፖራ ግንኙነት መመስረትና ተሳትፎውን ማሳደግ የሚኖረውን ጉልህ ሚና ግምት ውስጥ አስገብቶ የተቀረጸ በመሆኑ መንግስት በውጭ የሚኖረውን የህብረተሰብ ክፍል/ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን/ በሚገኙባቸው አገሮች መብታቸው ተጠብቆ እንዲኖሩና ከትውልድ አገራቸው የሚያስፈልጋቸውን አገልግሎቶች በኢምባሲዎችና ቆንስላ ጽ/ቤቶች በኩል እንዲያገኙ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል በማለት ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

የዳያስፖራ ፖሊሲው ዋና ዓላማ በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከትውልድ ሀገሩ ጋር ያለውን ትስስር በማጠናከር በአገሩ ልማት፣ ሰላምና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ጠንካራ ተሳታፊ ሆኖ ራሱን ጠቅሞ ትውልድ አገሩንም በመጥቀም በጋራ ማደግ የሚያስችል አመቺ ሁኔመፍጠር መሆኑን ኃላፊው አክለው ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ኃላፊው እንደገለጹት የክልሉ መንግስት በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን በክልላቸው በተለያዩ የልማት መስኮች የሚያደርጉትን ተሳትፎ ለማሳደግ የሚደረገውን ድጋፍ ለማጠናከር እንዲቻል በርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የዳያስፖራ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት መደራጀቱን ገልጸው በየደረጃው የሚገኘው የኢንቨስትመንት መዋቅር ዳያስፖራው በውጭ አገር ቆይታው ያፈራውን ሀብት በክልሉ ውስጥ በተለያዩ ኢንቨስትመንት እንዲሳተፉ በማድረግ ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል እንዲፈጥሩና የውጭ ምንዛሬን እንዲያሳድጉ ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

 
Content View Hits : 8228773

Comments

  • I loved as much as you will receive carried out ri...
  • What's up to all, it's actually a golod for me to ...
  • Hello there! This is my frst visit to your blog! W...
  • Hello there! This is my frst visit to your blog! W...
  • Quality posts is the secret to interest the users ...

Latest News

Who is online

We have 37 guests online

Entertainment