የፌዴራል አቃቤ ሕግና የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረጉ

E-mail Print PDF

የፌዴራል አቃቤ ሕግና የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረጉ
የኢፌዴሪ የመንግስት ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በወንጀል ተጠርጥረው የተከሰሱና ጉዳያቸው በፌዴራል ደረጃ ሲታይ የነበረ 598 ተከሳሾችን ክስ ማቋረጡን የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር ምክር ቤት ደግሞ 2 ሺህ 905 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ጠቅላይ አቃቤ ሕግና ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍርዴ ቸሩ እንደገለጹት ባለፉት ሁለት እና ሶስት ዓመታት በክልሉ ተከስተው በነበሩ ግጭቶች በወንጀል ተጠርጥረው በፌዴራል ደረጃ ምርመራ የተጣራባቸው፣ ክሣቸው በሂደት ያለ እና ፍርድ የተወሰነባቸው 598 ሰዎች መንግስት በወሰነው ውሣኔ መሠረት የፌዴራል አቃቤ ሕግ ክሣቸው እንዲነሣ ወስኗል፡፡

ምንም እንኳ በተለያዩ ጊዜያቶች በተለያዩ ደረጃ በወንጀል መሣተፋቸው ቢረጋገጥም ክሣቸው ተቋርጦ መዝገቡ እንዲዘጋ ለየፍርድ ቤቶች የክስ ማንሻ ደብዳቤ ተላልፏል ብለዋል፡፡

አቶ ፍርዴ አክለውም የክልሉ መንግስት በዓመት ሁለት ጊዜ ለሕግ ታራሚዎች ይቅርታ ያደርጋል፡፡ በመሆኑም ግማሽ ዓመቱን መሠረት በማድረግ 2,923 ሕግ ታራሚዎች ጉዳያቸው ተጣርቶ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት ከጥር 23 ቀን 2010 . ጀምሮ ይቅርታ እንዲደርግላቸው ወስኗል፡፡

 

የይቅርታ አሰጣጡ ፍትሃዊና ከአድሎ የፀዳ እንዲሆን መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡ በዚህ መሠረት የታራሚዎች የቆይታ ጊዜ፣ የዕድሜ መግፋት፣ በቆይታ ጊዜያቸው የተፀፀቱ መሆኑን፣ እንዲሁም በግድያና በግድያ ሙከራ የተሣተፉ ደግሞ ከተጎጅ ቤተሰቦች ጋር መታረቃቸው የቴክኒክ ኮሚቴው ካረጋገጠ በኋላ መስፈርቱን ላሟሉት ይቅርታ ተሰጥቷል ያሉት አቶ ፍርዴ ዘር ማጥፋት፣ ሙስና፣ አስገድዶ መድፈር፣ ሕገ-ወጥ የመሣሪያ ዝውውር እና መሰል ወንጀሎች በሕገ-መንግስቱ ይቅርታ የማያሰጡ ናቸው ብለዋል፡፡

 
Content View Hits : 8228777

Comments

  • There's definately a great deal to find out about ...
  • I loved as much as you will receive carried out ri...
  • What's up to all, it's actually a golod for me to ...
  • Hello there! This is my frst visit to your blog! W...
  • Hello there! This is my frst visit to your blog! W...

Latest News

Who is online

We have 31 guests online

Entertainment